አብዛኞቻችን ኑዛዜን የምንረዳው እኛ ከዚህ አለም ስናልፍ ሀብታችንን ለቀሪው ቤተሰባችን የምናስተላልፍበት
መንገድ ብቻ እንደሆነ አድርገን ነው። እንደውም አብዛኞቻችን ብዙ ግዜ እኔ ኑዛዜ ምን ያድርግልኛል
የማሰተላልፈው ሃብት ንብረት የለኝ እንላለን። እረ እንደውም ካላረጀን ወይም አይበለው እና በጸና በሽታ
ካልተያዝን ትዝም አይለን። ታስታውሱ እንደእሆነ፤ ኮቪድ አለምን ባስጨነቀ ግዜ ስንቶቻችን ነበር ስለ ኑዛዜ
እና ተያያዥ ሰነዶች ጉዳያችን አርገን ስናዘጋጅ የነበረው? ስለ ነገ አስቦ መዘጋጀት አስገዳጅ በሆኑ ምክንያት
ብቻ የሚደረግ ወይም ለጠንቃቃ ሰው ብቻ የተሰጠ ችሎታ አይድለም። ሁላችንም ግዜ ውስደን ዛሬ
ልንፈጽመው የምንችለው በጣም ቀላል ነገር ነው። ማንም ስለ ዛሬ እንጂ ስለ ነገ አያውቅም እና ነገን ዛሬ
ማቀድ ብልህነት ነው።
እዚህ በምኖርባት የኤልኖይ ግዛት ኑዛዜ ሲዘጋጀ ከሌሎችህ ተጨማሪ አባሪ ሰነዶች ጋር መሆን አለበት።
እነዚህ አባሪ ሰነዶችህ የአንድ ሰው የጤና አገልግሎት፣ የገንዘብ አስተዳድርን እና የንብረት ክፍፍልን
በተመለከተ የእርሱን ፍላጎት የሚያመላክትበት እና ለአፈጻጸሙም መመሪያ የሚሰጥበት ነው። ለምሳሌ
በአንድ መጥፎ አጋጣሚ አንድ ሰው በተለያየ ምክኛት ፍላጎቱን መግለጽ በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ቢገባ
እርሱን ወክሎ የሚፈልገውን የህክምና አገልግሎት አይነት የሚያስረዳ ሰው በሰነድ ካልሾመ ቤተሰብም ምንም
አይነት ውሳኔ ወይም አስተያየት ሰለ እርሱ መስጠት አይችሉም። ስለሆነም ከወዲሁ በእደዚህ አይነት ሁኔታ
ውስጥ ሲሆኑ ምን አይነት የህክምና እርዳታ እንዲደረግሎ እንደሚፈልጉ እና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ
የእርሶን ፍላጎት የሚውስንሎትን ሰው ከወዲሁ በ Durable Power of Attorney for Healthcare
ማዘጋጀት ብልህነት ነው።
በተጨማሪም አንድ ሰው በተለያየ ምክያት ፍላጎቱን መግለጽ በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ቢገባ እንደርሱ ሆኖ
የፍይናንስ ጉዳዮቹን የሚፈጽምለት ለምሳሌ የባንክ አካውንቱን የሚያንቀሳቅስለት፣ ቢሎችን የሚከፍልለት፤
ንብረቱን የሚያስተዳድርለት ሰው ጤነኛ በሆነ ግዜ ካልሾመ እንደዚህ አይንት ጉዳይ በሚያጋጥምበት ግዜ
ግዴታ ፍርድ ቤት ብቻ ነው ሊሾም የሚችለው። ይህም ለተጨማሪ ወጪ የሚዳርግ፤ የተንዛዛ፤
ለአለመግባባት በር የሚከፍት ነው። ከዚህ ሁሉ ለመዳን Durable Power of Attorney for
property/Financial Power of Attorney አሁን በግዜ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።
ሌላው በጣም አስፈላጊ ሰነድ Living will ይባላል። ይህ ሰነድ እንደው አይበለው እና ህይወቶ በሞት እና
በህይወት መካከል ብትሆን ህይወቶን ለማስቀጠል ምን አይነት የህክምና እርዳታ እና ማሽኖች
ቢገጠምሎ/ባይገጠምሎ እንደሚፈልጉ ለጤና ባለሞያዎች እና ለወዳጅ ዘመድ ፍላጎቶን የሚገልጹበት ሰነድ
ነው።
እነዚሀን እና መስል የውርስ ሰነዶችን ለማዘጋጀት ወደ ቢሮአችን በ (224) 584-8086 ቢደውሉ ወይም
በኢሜል አድራሻችን tworkneh@worknehlaw.com መልእክቶን ቢያደርሱን ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን።